






የመሶብ የአንድ መዐከል አገልግሎት ሠራተኞችና አመራሮች
የፀረ ሙስና ቀን በተለያዩ ሁነቶች አከበሩ
ሙስናን በፅናት በመከላከል
መልካም አስተዳደርን
እናረጋግጥ!
"Let's guarantee good governance by resolutely fighting corruption!
በ2018ዓ.ም
ኮሚሽነሩ
ከም/ጠቅላይ ሚኒስተር ሰርትፊኬትና
የዋንጫ ሽልማት
ሽልማት ሲረቡ
ኮሚሽነር ሐብታሙ ሞገስ
የአማራ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር
ኮሚሽነር ማሩ ቸኮል
የአማራ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር
በ2017ዓ.ም
ኮሚሽነሩ
ከክቡር ፕሬዚዳንት የሰርትፊኬት ሽልማት ሲረከቡ
ሊንኩን በመጫን
ሀብትዎን ያስመዝግቡ!
የአማራ ክልል የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን
የአማራ ክልል የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽኑን እንደገና መልሶ ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 237/2008 መሠረት የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም እና በስሩ ደሴ ጎንደር ደ/ብርሀን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን እንዲሁም የዞን ፣የወረዳ እና የተቌማትን የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎችን በማደራጀት እና በመምራት የሥነ ምግባር ግንባታ እና የፀረ-ሙስና ትግሉን አሳታፊ በሆነ መንገድ የሚመራ መንግስታዊ ተቋም ነው፡ ኮሚሽኑ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አስቸኳይ የሙስና መከላከል፣የተቐም የአሰራር ስርዓት ጥናት ሀብት ምዝገባ እና የማሳወቅ ስራን ማከናወን አንዱ ተግባር ነው፡፡ ተቐማት አሰራራቸው ከሙስናና ብልሹ አሰራር የፀዳ ይሆን ዘንድ በትኩረት የምንሰራ ሲሆን በተጨማሪም ሀብትን ማሳወቅና ማስመዝገብ የመንግስትን አሰራር በግልፅነትና በተጠያቂነት ለመመስረት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ተመራጮች፣ ተሿሚዎችና የሚመለከታቸው የመንግሥት ሠራተኞችን ሀብትና ጥቅማቸውን እንዲያሳውቁ፣ እንዲያስመዘግቡና እንዲያሳድሱ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የዘጠኝ ወር የዕቅድ ክንውን አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ጥምረት
ከፍትህ አካላት ባለሙያዎችና አመራሮች ጋር ተካሄደ መድለክ
ከሚዲያ ተቋማት አመራሮች ጋር ተካሄደ መድለክ
የሥምምነት ሠነድ ተፈራርመናል
በአመራሩ የሙያ ሥነ ምግባር እና ብልሹ አሰራር ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሥምምነት ሠነድ ተፈራርመናል
ከሚዲያ ባለሙያዎችና አመራሮች ጋር ተካሄደ መድለክ
የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዋናዋና ተግባራት

አቶ ገበየሁ ጥሩሰው
የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ትምህርትን በማስፋፋት፣ ሙስናና ብልሹ አሰራርን የማይሸከም ህብረተሰብ መገንባት ነው፡፡

አቶ ፋሲል አለኸኝ
የተቋማትን የአሠራር ስርዓት በጥናት በመለየት ሙስናና ብልሹ አሠራርን አስቀድሞ መከላከል፣

አቶ ይልቃል ወርቅነህ
ሀብት ንብረታቸውን የማስመዝገብ ግዴታ የተጣለባቸውን ተመራጮች፣ ተሿሚዎች እና የመንግስት ሠራተኞች ሀብት መመዝገብ እንዲሁም የሀብት ምዝገባ ትክክለኛነትን የማረጋገጥ እና የግልፀኝነት አሠራርን ማስፈን ነው፡፡

አቶ ሞገስ ወርቁ
የኮሚሽኑን ዓላማ ወይም ግብ ለማሳካት አስቀድሞ የሚዘጋጅ ዝርዝር መመሪያ፣ የድርጊት መርሃ-ግብር ወይም ፍኖተ-ካርታ ማለት ነው።

ኮሚሽነር ሀብታሙ ሞገስ
የአብክመ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ከምስራቅ አማራ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና ሠራተኞች ጋር የሥራ ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱ በ2019 የበጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በትብብር፣ በተጠያቂነትና በተቀናጀ አሰራር ለመስራት የጋራ መግባባት የተደረሰ መሆኑን ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል።
- All
- Gallery Item

የኮሚሽኑ ተጠሪዎች
ከኮሚሽኑ ዳይሬክቶሬቶች ዉስጥ ከድጋፍ ሰጭ ዳይሬክቶሬቶች መካከል “የኮሚሽኑ ተጠሪዎች” 1ኛ ደረጃ በመዉጣት የሰርትፍኬት ሽልማት አገኙ!!
ሙስና
በስልጣን፣ በኃላፊነት ወይም በአደራ የተሰጠንን ቦታ ለግል፣ ለቡድን ወይም ለቤተሰብ ጥቅም ማዋልን የሚያመለክት ህገ-ወጥ እና የሞራል ብልሽት ተግባር ነው። ይህ ድርጊት በአገራት የኢኮኖሚ ዕድገት፣ በማኅበራዊ ፍትህ እና በሕግ የበላይነት ላይ ከፍተኛ ቀውስ ያስከትላል።
ዋና ዋና የሙስና ዓይነቶች (Forms of Corruption)
ጉቦ (Bribery): ለአንድ አገልግሎት ወይም ጥቅም ሲባል በገንዘብ፣ በንብረት ወይም በዓይነት የሚደረግ ህገ-ወጥ ስጦታ።
ምዝበራ (Embezzlement): ለሕዝብ ወይም ለድርጅት ሥራ የተመደበን ገንዘብና ንብረት ለግል ጥቅምና ፍላጎት ማዋል።
ዘመድ አዝማድ መጥቀም (Nepotism): የሥራ ቅጥርን፣ እድገትን ወይም የጨረታ ዕድሎችን ብቃትን መሠረት ሳያደርጉ ለቤተሰብና ለቅርብ ወዳጆች መስጠት።
የስልጣን አላግባብ መጠቀም (Abuse of Power): የተሰጠንን ኦፊሴላዊ ስልጣን ተገቢ ባልሆነ መንገድ ሌሎችን ለመጉዳት ወይም ራስን ለመጥቀም ማዋል።
የጥቅም ግጭት (Conflict of Interest): የአንድ ግለሰብ የግል ፍላጎት ከሙያዊ ወይም ከሕዝባዊ ኃላፊነቱ ጋር መጋጨት።
ርዕይ2022 በላቀ የሥነምግባር ግንባታ ከሙስና የፀዳ ክልል!!
ተልዕኮየተቋማት የሥነምግባር እሴቶች ብቃትና
የአሠራር ሥርዓት ግልጽትና ተጠያቂነት በመከታተልና በማረጋገጥ፤
የሙስና ተጋላጭነት ሥጋት በዘላቂነት ማስወገድ፣
ዕሴቶችየመልካም ሥነ ምግባር ተምሳሌት
አገልጋይነት
ሙያዊ ብቃት
ምርምርና ፈጠራ
ግልጽነትና ተጠያቂነት
ቅንጅታዊ አሰራር
የኮሚሽኑ መርሆዎችግልጽነት እና ተጠያቂነት
ትብብርና አጋነት
አሳታፊነት
ሙያዊ ብቃት
የተሰጠዎትን መግቢያ ኮድ (Username/Password) በትክክል ይጠቀሙ!








