Latest News

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተመሠረተበትን 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በድምቀት ተከበረ።

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር

ሳሙኤል ኡርቃቶ(ዶ/ር)

25ኛ ዓመታችንን ስናከብርም ጠንካራና ደካማ ጎኖቻችንን ነቅሰን በማውጣት በቀጣይ የተሻለ ሥራ ለመሥራት ዝግጁነታችንን እያረጋገጥን ነው ብለዋል። ኮሚሽኑ የሙስና እና የብልሹ አሰራር ችግሮችን በመፍታት፣ ተጠያቂነትን በማስፈንና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመራቸውን ተግባራት ለማሳለጥ በሚያስችል ጠንካራ ቁመና ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። በተለይም ከሀብት ምዝገባ አንጻር አዎንታዊ ለውጦች መኖራቸውን ያነሱት ምክትል ኮሚሽነሩ፣ ሀብታቸውን ባላስመዘገቡ አካላት ላይ ተጠያቂነትን የማስፈን ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። የፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው ከሚሽኑ ባለፉት አመታት በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ በርካታ ተግባራት ማከናወኑን ገልፀው፤ በቀጣይም አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሥልጠና መሰጠቱን ጠቁመው፤ በሚቀጥለውም ዓመትም ለአዳዲስ የፖርላማ አባላትን ለማሰልጠን እቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡ በመድረኩ ኮሚሽኑ በ25 ዓመቱ የፀረ-ሙስና ትግሉ ትናንት፣ ዛሬ እና ነገን ላይ ትኩረት ያደረገ ሰነድ እና ዶክመተሪ ፕሮግራም ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። በመርሃ ግብሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ እንዲሁም አበላት፣ በፌደራል፣ በክልል እና ከተማ አስተዳደር የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያገለገሉ የቀድሞ ኮሚሽነሮች፣ በኮሚሽኑ ከ20 ዓመት በላይ ላገለገሉ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሰራር!

17ኛው አገርዓቀፍ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ዝግጅት ላይ ግምገማዊ ውይይት ተካሂዷል።

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር

የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ሲያቀርቡ:: ሐብታሙ ሞገስ (ኮሚሽነር)

17ኛው አገርዓቀፍ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ዝግጅት ላይ ግምገማዊ ውይይት ተካሂዷል።
አገርዓቀፍ የትስስር ጉባኤው በ2018 በጀት አመት በሥነምግባር ግንባታ፣ በሙስና ቅድመ-መከላከል፣ በተቋማዊ ማስፈጸም አቅም ግንባታ ጋር በተያያዘ ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥና ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ ስምምነት በመፍጠር የተቀናጀ ዘርፍ ተኮር የፀረ-ሙስና ትግል በውጤታማነት ተግባራዊ እንዲሆን ምቹ ሁኔታን መፍጠሩ ተመላክቷል፡፡
በጉባኤው የአገር ዓቀፍ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በትስስር ጉባኤው በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የትውልድ ሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል እና በተቋማዊ ማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራዎች በአፈጻጸም የታዩ ጠካራ ጎኖችና ክፍተቶች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል፡፡
በ2019 በጀት ዓመትም በትውልድ ሥነምግባር ግንባታና ሙስናን አስቀድሞ መከላከል ፕሮግራም፣ የፀረ-ሙስና ትግል ተቋማዊ ቅንጅት፣ ትብብርና ትስስር ማጎልበት ፕሮግራም እንዲሁም በተቋም ግንባታ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡
በትስስር ጉባኤው የፌደራል፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ ም/ኮሚሽነሮች እና የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሰራር!

የአብክመ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የክልል፣ የዞን፣ ከተማ አስተዳደርና የወረዳዎች የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎችን የ2018 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትዉዉቅ አካሂዷል።

በመጨረሻም በ2018 በጀት ዓመት ከክልል፣ ዞንና ከተማ አስተዳደሮች መካከል የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት የእውቅና ሰርትፍኬት ሽልማት ተበርክቷል

በመሆኑም ከክልል ተቋማት መካከል የአብክመ ገቢዎች ቢሮ፣ ከዞኖች መካከል የአዊ ብሔረሰብ ዞን እና ከከተማ አስተዳደሮች መካከል የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር 1ኛ ደርጃ በመዉጣታቸዉ የእዉቅና ሽልማቱ ባለቤት ሁነዋል።

 

photo_2026-08-20_23-23-15 (2)

 ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዞን፣ የከተማ አስተዳደር፣ የተቋማትና የወረዳዎች የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች፣ የተቋሙ ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላትና የአብክመ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነሮች በተገኙበት የ2018 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትዉዉቅ አካሂዷል።

 

ኮሚሽነሩ በ2018 በጀት አመት ዉጤታማ ስራ የታየበት ቢሆንም በ2019 በጀት ዓመት ደግሞ የነበሩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና የተሻለ ውጤት ለማምጣት ሁላችንም የጋራ መግባባትና ግንዛቤ መያዝ ያስፈልጋል በማለት በማጠቃለያ ንግግራቸው አሳስበዋል።

በመጨረሻም በ2018 በጀት ዓመት በተቋሙ ሂደቶች፣ ሰራተኞች፣ ዞን፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ የተቋምና የመስተዳድር የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች መካከል የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የእውቅና ሰርትፍኬት ሽልማት የተበረከተ መሆኑን ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል።

የአብክመ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከቅርንጫፍ ሰራተኞች፣ ከዞን ፣ ከወረዳና ከተቋማት የሥነ ምግባር ባለሙያዎች ጋር የአብክመ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነሮች በተገኙበት የ2018 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትዉዉቅ አካሂዷል።

photo_2026-08-25_23-06-34
photo_2026-08-25_23-06-34 (4)
photo_2026-08-25_23-06-34 (7)

አጠቃላይ የቅርንጫፉ ሪፖርትም በአቶ ረታ አሰግደዉ የቀረበ ሲሆን ለስራ ቡድኖች እና ባለሙያዎችም በአፈፃፀማቸው ዕውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷል።

ከስራ ቡድን 1ኛ የሃብት ማሳወቅና ማስመዝገብ፣ 2ኛ ደጋፊ የስራ ሂደት፣ 3ኛ የሥነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥልጠና ሂደት ሲሆኑ ከፈፃሚዎች 1ኛ ወ/ሮ እመቤት ገ/ሃና የሃብት ምዝገባ ባለሙያ፣ 2ኛ አቶ በቀለ ዘውዱ ጥበቃ እንዲሁም 3ኛ ወ/ሮ ራሄል ቀፀላ የሚዲያ ህትመት ባለሙያ በመሆን እዉቅናና ሽልማታቸዉ ከምክትል ኮሚሽነር ማሩ ቸኮል ተቀብለዋል።

የአብክመ የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምስራቅ አማራ/ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ባለሙያዎች፣ ለዞን፣ ለወረዳ፣ ለከተማ አስተዳደርና ለተቋማት የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች የሥነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል የአሰልጣኞች እየሰጠ ነዉ።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የዞንና የከተማ አስተዳደሮች፣ እንዲሁም የተቋማትና የወረዳዎች የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ተካሂዷል።

22ኛው የፀረ-ሙስና ቀን አከባበር​

ከተለያዩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት የተዘጋጁ አዳዲስ ዜናዎች

የግብረ ገብነት ግንባታ ባለቤቶች እና ሚናቸው

  • ቤተሰብ፡ ልጆችን ከመጀመሪያው ጀምሮ መልካም ነገር በማስተማር የሞራል መሰረት ይጥላል።
  • ትምህርት ቤቶች፡ ተማሪዎች በሥነ ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ ስልጠናዎችን እና የትምህርት ይዘቶችን ይሰጣሉ።
  • የህዝብ ተቋማት እና የሀይማኖት ተቋማት፡ ህጎችን በማክበርና እሴቶችን በማስተላለፍ ትክክለኛውን መንገድ ያሳያሉ።
ግንዛቤ ማስጨበጥ

ዋና ዋና ተግባራትግንዛቤ ማስጨበጥ፡ ለብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ተማሪዎች የሥነ-ምግባር ስልጠናዎችን መስጠት።የትውልድ ግንባታ፡ አገር አቀፍና ህብረተሰባዊ እሴቶችን ማሳደግ እንዲሁም ሐቀኛ ዜጎችን ማፍራት።ሙስና መከላከል፡ ተቋማት ፍትሃዊ እና ከብልሹ አሰራር ነፃ በሆነ መንገድ እንዲሰሩ መቆጣጠር።

የትኩረት አቅጣጫዎች

ማህበራዊ ቀውሶችን ማስወገድ። ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ማፍራት። ተቋማዊ ሐቀኝነትን ማጠናከር

የሥነ ምግባርና ግብረ ገብነት ፋይዳ

ሰላም ማምጣት: ማህበራዊ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት። ኃላፊነት ስሜት: እያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል ለድርጊቱ እና ለአካባቢው ተጠያቂ መሆን። መልካም ባህርይ: መከባበርን፣ ታማኝነትን እና ትብብርን ማዳበር።

ኮሚሽኖች በሥነ ምግባርና ግብረ ገብነት ግንባታ ዙሪያ ማህበረሰቡን ከንጹህ አሰራር ጋር ለማስተዋወቅ፣ ስልጠናዎችን ለመስጠት እና ሙስናን ለመከላከል ሰፊ ስራዎችን ያከናውናሉ። ለምሳሌ የአማራ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ያሉ ተቋማት ወጣቶችን እና ተማሪዎችን በማሰልጠን መልካም ባህሪ እንዲኖራቸው ጥረት ያደርጋሉ።

ከምስራቅ አማራ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራርና ሠራተኞች ጋር የሥራ ውይይት ተካሄዱ።

  • አብክመ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀብታሙ ሞገስ ከምስራቅ አማራ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ደሴ ቅርንጫፍ  ጽ/ቤት ኃላፊና ሠራተኞች ጋር የሥራ ውይይት አካሂደዋል።
  • በውይይቱ ወቅት ተቋሙ ከተቋቋመበት ዓላማና ተልዕኮ አንጻር ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ከቁልፍ እና ዓበይት ተግባራት ላይ በስፋት ተወያይተዋል።
  • በተጨማሪም በሥራ አፈጻጸም ላይ እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ አማራጮች ተዳሰው፣ ተቋሙ የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግብ የሚያስፈልጉ የትብብር አቅጣጫዎች ላይ ግልጽ መግባባት ተደርሷል።
  • በዚሁ ወቅት የምስራቅ አማራ ደሴ ቅርንጫፍ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም አያሌው፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ የቻለው ኮሚሽኑ በየጊዜው ባደረገው የቅርብ ድጋፍ፣ ክትትልና ሙያዊ መመሪያ ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።
  • አቶ አብርሃም አክለውም፣ በ2019 የበጀት ዓመት ከኮሚሽኑ፣ ከመንግሥት ተቋማት፣ ከሁሉም ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በተጠናከረ ቅንጅት በመስራት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስረድተዋል።
  • በመጨረሻም ኮሚሽነር  ሀብታሙ ሞገስ፣ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አመራርና ባለሙያዎች መካከል ያለውን  የሥራ ቅንጅትና ቁርጠኝነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ፣ በቀጣይም የተቋሙን ተልዕኮ በብቃትና በከፍተኛ ትጋት በመፈጸም የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
  • በውይይቱ በ2019 የበጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በትብብር፣ በተጠያቂነትና በተቀናጀ አሰራር ለመስራት  የጋራ መግባባት የተደረሰ መሆኑን ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል።

“ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር !”

Scroll to Top